Welcome to the Ethiopian Orthodox Tewahedo Church of Tanzania, Se'alite Mihret Saint Mary Church.

Support the Church

በታንዛንያ የመጀመሪያዋን የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን አብረን እንገንባ!

“አሁንም እንሆ እግዚአብሔር ለመቅደስ የሚሆን ቤትን ትሠራ ዘንድ መርጦሃልና ጠንክረህ ፈጽመው”
1ኛ መ. ዜና 28:10

ለረጅም ጊዜ በታንዛንያ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ሕጋዊ እውቅናም ሆነ የራሷ ሕንጻ ቤተክርስቲያን አልነበራትም። በተለያየ ምክንያት ወደ ታንዛኒያ በየጊዜው በመጡ ምእመናን የተደረጉ ጥረቶች ፍሬ አፍርተው የእግዚአብሔር ፈቃድ ሲሆን በታንዛንያ ዳሬሰላም የመጀመሪያ የሆነውን የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ን ለመስራት አስፈላጊ ከሆኑ ቅድመ ሁኔታዎች ውስጥ ዋና ዋና ሂደቶችን አልፈን ከታንዛኒያ መንግስት የእውቅና ፈቃድ በማግኘት እንዲሁም በብፁዕ አቡነ ማቴዎስ የሰሜን እና ምስራቅ አፍሪካ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ እና የቅዱስ ሲኖዶስ አባል መልካም ፈቃድ፣ መመሪያ እና ቡራኬ መሰረት የታንዛኒያ ሰአሊተ ምሕረት ቅድስት ማርያም ቤተክርስቲያን ለመስራት የሚያስችሉ መሠረታዊ ሥራዎችን ጀምረናል።

ነገር ግን በሀገረ ታንዛኒያ የሚኖረው ምዕመን ቁጥር አነስተኛ እና ጊዜያዊ ሰራተኛ የሚበዛበት በመሆኑ በነዋሪው ምዕመን ሙሉ ወጪ ሸፍኖ የቦታ ግዥ መፈጸም እና ግንባታ መስራት አስቸጋሪ ሆኖብናል። ስለሆነም እርስዎም በዚህ ታላቅ ታሪካዊና መንፈሳዊ ተልዕኮ እርዳታ እንድታደርጉልን በእግዚአብሔር ስም ጥሪያችንን እናቀርባለን።

❖ የተወሰኑ ምዕመናን ወደ ግሪክ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን በመሄድ የጸሎትና ሌሎች የአምልኮ ሥርዓቶችን (የክርስትና ጥምቀትን ጨምሮ) ሲፈጽሙ እንደነበር ምእመናን ይገልጻሉ ያመለክታሉ።

❖ አብዛኛው ምዕመን በየቤቱ የግል ጸሎት በማድረግ መንፈሳዊ ሕይወቱን ለመምራት ይሞክራል፤ ቀላል የማይባል ቁጥር ያለው ምእመን ደግሞ ከቤተክርስትያን እርቆ ይገኛል።

❖ የግሪክ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን ቀደም ሲል በየሳምንቱ እሁድ አዳራሿን ለጋራ ጸሎት በነጻ ትፈቅድ የነበረ ቢሆንም፣ ከመጋቢት ወር 2017 ዓ.ም. ጀምሮ አዳራሹን ለመጠቀም በቀን 50 ሺህ የታንዛኒያ ሽልንግ እንዲከፈል በመደረጉ፣ ምዕመናን ይህንን ክፍያ እየፈጸሙ በዩቲዩብ የሚተላለፈውን የቅዳሴ ሥነ ሥርዓት በጋራ እየተከታተሉ ይገኛሉ።

ወቅታዊ የቅዳሴ አገልግሎት፡-

❖ የሥርዓተ አምልኮ ችግሩን በተወሰነ ደረጃ ለመቅረፍ፣ በተለይም ምዕመናን ቅዱስ ቁርባን እንዲቀበሉና ሕፃናት የክርስትና ጥምቀት እንዲያገኙ ለማድረግ፣ በዓመት ሁለት ጊዜ (በደብረ ዘይት በዓልና በፍልሰታ ጾም ወቅት) ከምሥራቅ አፍሪካ ሀገረ ስብከት ጋር በመነጋገርና በምዕመናን ሙሉ ወጪ ካህናት ከዩጋንዳ እየመጡ መንፈሳዊ አገልግሎት እንዲሰጡ እየተደረገ ይገኛል።

❖ ይህም ማለት አንድ ልጅ ሲወለድ የክርስትና ጥምቀት የሚያገኘው በእነዚህ ሁለት ጊዜያት ብቻ ነው፣ ምዕመናንም ቅዱስ ቁርባኑን ለመቀበል ቢፈልጉ እነዚህን ቀናት መጠበቅ ግዴታቸው ሆኗል። በእነዚህ ጊዜያት በተለያዩ ምክንያቶች (ለምሳሌ በሴቶች ወርሃዊ ልማድ ወይም በሥራ ምክንያት ሌላ ቦታ መሆንን ጨምሮ) አገልግሎቱን ማግኘት ካልተቻለ ደግሞ ሌላ ተጨማሪ ጊዜ መጠበቅ ግዴታ ነው።

❖ ከዩጋንዳ በሚመጡ ካህናት የቅዳሴና ሌሎች የአምልኮ ሥርዓቶች መካሄድ መጀመራቸው፣ ልጆቻቸውን በግሪክ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን ያስጠምቁ ለነበሩ ምዕመናን የተወሰነ እፎይታ የሰጠ ቢሆንም፣ አገልግሎቱ በሚፈለገው መጠንና ቀጣይነት ባለው መልኩ ሊከናወን አልቻለም።

አብረን እንገንባ!
የእርስዎ ድጋፍ ለቀጣዩ ትውልድ መንፈሳዊ ቅርስ ይሆናል።

The Spiritual Wilderness

No Place to Worship

For years, our community has been scattered without a dedicated church building to celebrate holy days or observe traditional services.

Sacramental Needs

Without a church, children cannot receive Baptism on time, and believers cannot partake in the Holy Communion, the heart of our life.

Building Community

We are striving to build a permanent home where our traditions are preserved, and our faith is strengthened for generations to come.

Worship Schedule

Divine Liturgy (Kidasse)

Twice a year, through priests sent by our mother church, the Holy Communion service is conducted with great reverence. These are the special times of the service:-

. The Feast of Debre Zeyit

. A day selected during the period of Lent.

During these times, the faithful repent and have the opportunity to receive the Holy Communion, as well as to partake in other sacraments of the Church.

Weekly Prayer Schedule

Every Sunday morning from 6:00 AM until 11:00 AM.

A communal service of prayer, hymn singing, and Gospel teaching is offered. This practice allows the faithful to come together at the end of the week to worship their Creator in unity and to engage in prayer.

Monthly Feast Days

The Monthly Feast of Our Lady, Saint Virgin Mary

On the 21st day of each month, or on the first Sunday following the 21st, the feast of Our Lady is celebrated with a special liturgical program by the community.

yearly Feast Days

Saints' Commemorations

In addition to the above-mentioned Holy Communion services, the following major annual feasts are celebrated by the faithful with collective participation and great reverence:

• Nativity: The Feast of the Birth of our Lord and Savior Jesus Christ is celebrated every year on December 29.

• Baptism (Timkat): The Feast of the Baptism of our Lord is celebrated every year on January 19.

• Hosanna (Palm Sunday): The Feast of Hosanna is celebrated at the beginning of Holy Week.

• The Birth of Our Lady: The Feast of the Birth of our Lady, Saint Virgin Mary, is celebrated every year on May 9.

• Mount Tabor (Transfiguration): The Feast of the Transfiguration of our Lord, when His divine glory was revealed, is celebrated every year on August 20.

All these liturgical practices greatly contribute to strengthening the faith of the faithful, encouraging them to pray regularly, and enabling them to actively participate in their communal life.